
ሰላላም
poprap
ሰላም ለኢትዮጵያየ ለዉቧ አድባር፣ ሰላም ለባለብዙ ቀለማት ምድር፣ ለሰሜኗ ጥጥ ፈታይዋ እናቴ፣ ለደቡቡ በሽመና ለተካነው አባቴ፣ ለምስራቁ ልብስ ሰፊዉ አጎቴ፣ ለምእራቧ ጥለት ሰሪዋ አክስቴ፣ ሰላም ለኢትዮጵያየ ለዉቧ አድባር፣ ሰላም ለባለብዙ ቀለማት ምድር፣ ለመሃል አገር ነዋሪው አያቴ፣ ለእምየ ለተቀበረባት አትብቴ፣ አድጌ ለቦረቅኩባት መሰረቴ፣ ዘርቼ ለቃምኩባት መሬቴ። ሰላም ለኢትዮጵያየ ለዉቧ አድባር፣ ሰላም ለባለብዙ ቀለማት ምድር፣ አንድነት ለሴም፣ ለኩሽ መንደር፣ እዲያብብ መተሣሠብና ፍቅር፣ ሰላም ለኢትዮጵያየ ለዉቧ አድባር፣ ሰላም ለባለብዙ ቀለማት ምድር።